Supporting information for parents (Amharic)

ለወላጆች አጋዥ መረጃ - ቦሎህ፡ የጥቁር፣ እስያና የአናሳ ጎሳ ቤተሰብ ኮቪ -19 የእገዛ መስመር

ስለ ቦሎህ የእገዛ መስመር

የቦሎህ የእርዳታ መስመር ከብሔራዊ የድንገተኛ አደጋዎች ትብብር በበርናርዶ ጥቅምት 1 ቀን የተጀመረው አገልግሎት ነው፡፡ የእርዳታ መስመሩ ባልተመጣጠነ ሁኔታ በተጎዱት በጥቁር፣ በእስያና አናሳ በሆኑ የጎሳ ማህበረሰቦች ላይ በተከሰተው ወረርሽኝ ላይ ለተነሳው ምላሽ መስጫ ነው፡፡

የእገዛ መስመር ሰራተኞች ወይ ጥቁር፣ ኤሺያና አናሳ የጎሳ ማህበረሰብ ናቸው፣ ወይም የቀደመ ለልጆች፣ ለወጣቶችና ለቤተሰቦቻቸው አገልግሎቶችን የማቅረብ የቀደመ የሙያ ልምድ ያለው ከእነዚህ ማህበረሰቦች

እንዴት መርዳት እንችላለን?

እርስዎ በኮቪድ -19 የተጎዱ ጥቁር፣ ኤሺያዊ ወይም አናሳ ጎሳ፣ ወጣት፣ ወላጅ ወይም እንክብካቤ አድራጊ ነዎት? አዎ ከሆነ ሀዘን፣ ኪሳራ፣ ሥራ አጥነት፣ የገንዘብ ችግር፣ ስለ ልጅዎ ትምህርት ወይም የወደፊት ሁኔታ፣ ስለ ጓደኛዎ ወይም ስለቤተሰብዎ፣ ቤት በመቆየትዎ ጭንቀትና ድብርት የተሰማዎት ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ከነዚህ በተጨማሪ ስለሌሎች ጉዳዮች ይጨነቁ ይሆናል፡፡ በዚህ ጊዜ ስለ ሚያሳስቦ ጉዳይ  ፣ ችግሮችዎ እና ጭንቀቶችዎ ሊያነጋግሩን የሚችሉ ሲሆን ተጨማሪ እርዳታ ለሚሰጡ ሌሎች ድርጅቶች የሞራል ድጋፍ፣ ተግባራዊ ምክርና ምልክት መስጨዎችን ማቅረብ እንችላለን፡፡

እኛ የምንሰጠው ድጋፍ ለእርስዎ እና ለሚንከባከቡት ልጅ (ልጆች) ነው፡፡ በድረገጻችን ላይ በሚገኘው ዌብቻት በኩል ወደ እኛ ጋር መደወል ወይም ከእኛ ጋር መወያየት ይችላሉ፡፡ የእርስዎን ዝርዝር መረጃ ከእኛ ጋር ማጋራት አያስፈልግዎትም ነገር ግን ወደ ቡድናችን ሀኪሞች ወይም ለሌላ አገልግሎት ለመላክ ከፈለጉ መረጃዎን ወስደን ከእርስዎ ፈቃድ ጋር መጋራት ያስፈልገናል፡፡ እንዲሁም በበርካታ ጉዳዮች በድረገጻችን ላይ ጠቃሚ ምክሮችን ማግኘት ይችላሉ ፤ ለምሳሌ ስሜታዊ ደህንነት፣ ቤተሰቦችን መደገፍ፣ ሀዘን እና ኪሳራ፡፡

ከእገዛ መስመሩ ጋር ግንኙነት ሲያደርጉ ምን ይሆናል?

እርስዎ እና / ወይም ልጅዎ (ልጆችዎ) ስላጋጠሟቸው ነገሮች ሁሉ ከእርስዎ ጋር ከሚነጋገር  ወዳጃዊ የእገዛ መስመር አማካሪ ምላሽ ያገኛሉ፡፡ የእገዛ መስመር አማካሪው እርስዎን በማዳመጥ ስለሚፈልጉት እገዛና ምክር ዓይነት ውሳኔ ለመስጠት ድጋፍ ያደርግሎታል፡፡ በእርስዎ ስምምነት መሰረት የእገዛ መስመር አማካሪው ከእርስዎ ጋር በርካታ ጥሪዎች ሊኖሩት የሚችል ሲሆን ለእርስዎ በሚመች ጊዜ መልሶ ሊደውሉልዎት ይችላል፡፡

የእገዛ መስመር አማካሪው ለእርስዎ እና/ወይም ልጆችዎ የህክምና ባለሙያዎቻችን አንዱን እንዲያነጋግሩ ሊያዘጋጅልዎ የሚችል ሲሆን ስድስት የምክር ጊዜዎችን እንዲያካሂዱ እና አስፈላጊ ከሆነም ተጨማሪ የምክር ጊዜዎችን ሊያዘጋጅ ይችላል፡፡ በቤተሰብዎ ፍላጎቶችና ሁኔታዎች ላይ በመመርኮዝ በሳምንት አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ በስልክ የሚከናወኑ ክፍለ ጊዜዎች ይሆናሉ፡፡ የመጀመሪያው እና ስድስተኛው ክፍለ ጊዜ ቤተሰቡ ወይም ግለሰቡ በሚያጋጥሟቸው ሶስት ቁልፍ ተግዳሮቶች እንዲከናወን የመጀመሪያ መነሻ ምዘና ለመስጠት ለ 45 ደቂቃ ያህል ይሆናል ፣ በመጨረሻው ስብሰባ በአገልግሎቱ ወቅት የተከናወኑ መሻሻሎችን ለመወያየት እና ለማስገንዘብ ፡፡ በእያንዳንዱ ክፍለ ጊዜ የተገለጹትን ቁልፍ ተግዳሮቶች ለመቅረፍ እያንዳንዳቸው ከ 30 ደቂቃዎች እያንዳንዳቸው ከሁለት እስከ አምስት የሚደርሱ ክፍለ ጊዜዎች የህክምና ድጋፍን ያካትታሉ ፡፡

ድጋፍ በተለያዩ ቋንቋዎች ሊሰጥ ይችላል?

የእገዛ መስመራችን አማካሪዎች በእንግሊዝኛ፣ ኡርዱ፣ ሂንዲ፣ ሚርፉሪና ፑንጃቢ አገልግሎት መስጠት ይችላሉ፡፡ በታህሳስ 2020 ቋንቋዎቹ ቁጥር በማሳደግ አማርኛና ትግርኛን የሚያካትቱ ሲሆን አስተርጓሚዎችም በሌሎች ቋንቋዎች ሊሰጡ ይችላሉ፡፡ የሕክምናው ስብሰባዎች በሚቀጥሉት ቋንቋዎች ሊሰጡ ይችላሉ፡ እንግሊዝኛ፣ ቤንጋሊ፣ ሂንዲ፣ ፈረንሳይኛ፣ ፑንጃቢና ግሪክ፡፡

የጉዳይ ጥናት

እነዚህ የጉዳይ ጥናቶች የቦሎህ የእገዛ መስመር እንዴት ድጋፍ መስጠት እንደሚችል ምሳሌዎችን ይሰጣሉ፡፡

ማርታ በአካባቢው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የምትከታተል የሁለት ታዳጊ ልጆች እናት ናት፡፡ ማርታ ለ 15 አመት ወንድ ልጇ መጨነቅ የጀመረችው ኮሮናቫይረስን ላለመያዝ በመፍራት ትምህርቱን ለመከታተል ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነው፡፡ ማርታ ከልጅዋ አስተማሪ ጋር በዚህ ጉዳይ ላይ በመወያየት ድጋፍ ለማግኘት ስለፈለገች የቦሎህ የእርዳታ መስመር ቁጥር ተሰጣት፡፡

ማርታ የእርዳታ መስመሩን አነጋግራ የእገዛ መስመር አማካሪ የሆነውን ናዝ አነጋገረች፡፡ ማርታ የሚከተሉትን ለናዝ አጋርታለች፡ ‹‹ልጄ ጥቁሮች በኮቪድ የመሞት ዕድላቸው ከፍተኛ እንደሆነ ስለሰማ አሁን በጭንቀት እየተሰቃየ ነው፡፡ የምንሞት እየመሰለው እንደሆነ እየጠየቀን ሲሆን ወደ ትምህርት ቤት ለመሄድ ከቤት መውጣት አይፈልግም፡፡ በእውነቱ ስለ እርሱ ተጨንቀናል ምን ማድረግ እንዳለብንም አናውቅም፡፡›› ናዝ ከብዙ ጥሪዎች በኋላ ስለልጅዋ ስጋትና ፍርሃት ለመወያየት ከማርታ ጋር በመስራት በልጅዋ ሀሰብና ጭንቀቶች ላይ ለመነጋገር ከህክምና ባለሙያው ጋር የምክር አገልግሎት ለማግኘት ተስማማች፡፡ ማርታም ሆነ ልጇ ከሀኪም ጋር በተናጥል የምክር አገልግሎት ማግኘት ጀመሩ፡፡ የማርታ ልጅ በ Covid-19 ዙሪያ ጭንቀቱን ለመቆጣጠር በመንገድ ላይ ነው፡፡

የጉዳይ ጥናት

ካልሆን በፌስቡክ ገጹ ላይ የተለጠፈ ጽሑፍ ከተመለከተ በኋላ በዌብቻት ላይ የእገዛ መስመሩን አነጋግሯል፡፡ በመጀመሪያ እረፍት እንዲያደርግ የተደረገና በኋላም ክፍያው እንደቆመ ተናግሯል፡፡ የቤት ኪራይ ለመክፈል እና ለቤተሰቡ ምግብ መግዛት አለመቻሉ ያሳስበዋል፡፡ ከእገዛ መስመር አማካሪው ጋር በዌብቻት ውይይቱ ወቅት የእገዛ መስመር አማካሪውን ስለ ሁኔታው እንዲናገር ጠይቆታል፡፡ የእርዳታ መስመር አማካሪዋ ሳራ ካልሆንን አነጋግራ ስለሁኔታዎቹ ተወያዩ፡፡ ሳራ ሁሉንም መረጃዎች ወስዳ ከበርናርዶ እና ሌሎች ሊረዱ ከሚችሉ ድርጅቶች ጋር ጥቂት ጥያቄዎችን እንደምትጠይቅ ካልሆን ፈቃዱን እንዲሰጣት ተስማማች፡፡ ሳራ ካልሆን በሚኖርበት አካባቢ ያሉትን በርካታ አገልግሎቶችን አነጋግራ ካልሆንንና ቤተሰቡን ለመደገፍ በጣም የተሻሉ ዋና አገልግሎቶችን ለመለየት ጥረት አድርጋለች፡፡ ሳራ ለካልሆን ቤተሰቡ ድገጋፍ ማድረግ የሚችሉ በአካባቢው ያሉ በጎ  አድራጊዎች መረጃን ለካልሆን አጋርታለች፡፡

የእኛ ራዕይ የጥቁር፣ የእስያና አናሳ የጎሳ ልጆችና ወጣቶች ለተግዳሮቶች ምላሽ ለመስጠት ውስጣዊ ጥንካሬያቸውን ሲያሳድጉ ማየት ነው፡፡  ይህንን ራዕይ ለማሳካት ከእርስዎ ጋር አብረን መሥራት የሚያስደስተን ሲሆን ድጋፍ ከፈለጉ በሚከተለው አድራሻ እባክዎን ያነጋግሩ፡

ነፃ ስልክ፡ 0800 151 2605

ኢሜል፡ Boloh.helpline@barnardos.org.uk

ድረገጽ፡ https://helpline.barnardos.org.uk/