ከ11+ ለሆኑ ወደ ቦሎህ ፣ በርናርዶ የኮቪድ-19  የእገዛ መስመርና ዌብቻት እንኳን ደህና መጡ

በ 0800 1512605 ይደውሉልን ወይም በኢንተርኔት መስመር ላይ ይጻፉልን

እርስዎ በኮቪድ -19 የተጎዱ ጥቁር፣ ኤሺያዊ ወይም አናሳ ጎሳ፣ ወጣት፣ ወላጅ ወይም እንክብካቤ አድራጊ ነዎት? በዚህ ጊዜ ስለ ሚየሳስቦ ነገር ፣ ችግሮችዎ እና ጭንቀቶችዎ ሊያነጋግሩን የሚችሉ ሲሆን ተጨማሪ እርዳታ ለሚሰጧቸው ሌሎች ድርጅቶች የሞራል ድጋፍ፣ ተግባራዊ ምክርና ምልክት መስጨዎችን ማቅረብ እንችላለን፡፡

ባለሙያ ከሆኑ አብረው የሚሰሩትን ልጅ ወይም ወጣት እንዴት እንደሚደግፉ ለመወያየት እኛን ማነጋገር ይችላሉ፡፡

ያነጋግሩን

ከሰኞ-አርብ ከ 1ፒኤም - 8ፒኤም ለመነጋገር ዝግጁ ነን፡፡

በብቁ ቋንቋዎች ቦሎህ ማለት መናገር ማለት ነው፡፡

 በወረርሽኙ የተጠቁ ከሆነና ለማነጋገር ምክር ወይም ሰው ማናገር ከፈለጉ በ 0800 1512605 በምስጢር ሊደውሉልን ይችላሉ ወይም ደግሞ ከባለሙያ ድጋፍ ሰጪ አማካሪው ጋር በኢንተርኔት መስመር ላይ ለማነጋገር በስተቀኝ በኩል ባለው ዌብቻት ምልክት  ላይ በመጫን  ማግኘት ይችላለለ፡፡ ሰራተኞቻችን የእርስዎን ስልክ ወይም ዌብቻት ከሰኞ - አርብ፣ ከ 1ፒኤም - 8ፒኤም ይጠብቃል፡፡

የሀዘን፣ የጤና መታወክ፣ ቤት በመቀመጡ ድብታ ወይም መጨነቅ ከተሰማዎት፣ ገለልተኛነት ስሜት፣ ስለ ጓደኞች ወይም ስለቤተሰብ መጨነቅ፣ ስለገንዘብዎ፣ ሥራ አጥነት ችግር፣ ጉልበተኝነት ወይም ዘረኝነት መጠቃተ፣ የቤት እጦት ወይም ማፈናቀል ጉዳዮች ፣ ወደ ትምህርት ቤት / ዩኒቨርሲቲ ወይም ስለሌላ ጉዳይ ስለመመለስ ጭንቀት ካለቦት እኛ እዚ ያለነው እርሶን ለማገዝ ነው፡፡ የእኛ የልዩ የስነልቦና ሐኪሞች ቡድን በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ቀጣይነት ያለው ድጋፍ ሊሰጥዎ ይችላል፡፡

በስልክ ላይ የእኛ የእርዳታ መስመር አማካሪዎች በእንግሊዝኛ፣ በኡርዱ፣ በፑንጃቢ ወይም በሂንዲ ሊያነጋግሩዎት ይችላሉ፡፡

የእኛ የስነልቦና ሐኪሞች በእንግሊዝኛ፣ በሂንዲ፣ በቤንጋሊ፣ በፈረንሣይኛና በፑንጃቢ ቋንቋ የሕክምና ድጋፍ መስጠት ይችላሉ፡፡